{"title":"አዕምሯዊ የመማር ብልሐቶች የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት የማሻሻል ሚና፤ በሰባተኛ ክፍል ተተኳሪነት","authors":"Tsganesh Yosef, Hailay Tesfaye","doi":"10.59122/135108d","DOIUrl":null,"url":null,"abstract":"የጥናቱ ዓላማ አዕምሯዊ የመማር ብልሃቶች የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት የማሳደግ ሚና መፈተሽነው፡፡ ዓላማውን ለማሳካት በ2011 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ በጊዮርጊስ ትምህርት ቤት በመማር ላይ የሚገኙ የሰባተኛ ክፍልየአማርኛ ኢአፍፈት ተማሪዎች ሦስት መማሪያ ክፍሎች በአመቺ ንሞና ተመርጠዋል፡፡ ተሳታፊዎቹ በብልሃት 42፣ በብልሃትአልባ 38እና በቁጥጥር 38 በድምሩ 118 ሲሆኑ፣ በአንብቦ መረዳት ፈተናና በማንበብ ተነሳሽነት የፅሁፍ መጠይቆች አማካይነት መረጃሰጥተዋል፡፡ የተሰበሰበው መረጃ በገላጭና በድምዳሜያዊ ስታትስቲክስ (በባለሁለት ተላውጦ ልይይትና በባዕድ ናሙና ቲ-ቴስትተሰልቶ) ተተንትኗል፡፡ የጥናቱ ውጤቶችም በብልሃትና በብልሃትአልባ አቀራረቦች የተማሩት በተለመደው የማንበብ ትምህርትከተማሩት ይልቅ በአንብቦ መረዳት ችሎታቸው ጉልህ መሻሻል አሳይተዋል፡፡ ነገርግን በማንበብ ተነሳሽነት ላይ ጉልህ ሚና አላሳዩም፡፡በብልሃትና በብልሃት አልባው ቡድን መካከልም የአንብቦ መረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት ጉልህ ልዩነት እንደሌለ ተረጋግጧል፡፡ይህም ከሁለቱ የብልሃት አቀራረቦች አዕምሯዊ ብልሃትን በይዘትነትና በትግበራ መማርና በትግበራ ብቻ መማር ልዩነት እንደሌለውያሳያል፡፡ ስለዚህ ትግበራው በሁለቱም ቡድኖች ስለሚገኝ በይዘትነት ከመማር ይልቅ በትግበራ መማር አስተዋፅኦ እንዳለውያመለክታል፡፡","PeriodicalId":247662,"journal":{"name":"Ethiopian Journal of Business and Social Science","volume":"64 1","pages":"0"},"PeriodicalIF":0.0000,"publicationDate":"2020-12-01","publicationTypes":"Journal Article","fieldsOfStudy":null,"isOpenAccess":false,"openAccessPdf":"","citationCount":"0","resultStr":null,"platform":"Semanticscholar","paperid":null,"PeriodicalName":"Ethiopian Journal of Business and Social Science","FirstCategoryId":"1085","ListUrlMain":"https://doi.org/10.59122/135108d","RegionNum":0,"RegionCategory":null,"ArticlePicture":[],"TitleCN":null,"AbstractTextCN":null,"PMCID":null,"EPubDate":"","PubModel":"","JCR":"","JCRName":"","Score":null,"Total":0}
引用次数: 0